ምናሌ

ይህ ድር ጣቢያ ለአካባቢያዊ ደንበኞች ነው ፣ ሀገርዎ ከሌለ ዓለም አቀፍን ይምረጡ ፡፡

ሰለ አፍሪሬጂስተር

ሰለ አፍሪሬጂስተር ኤስ.ኤ

Aአፍሪሬጂስተር ኤስ.ኤ በ 2000 ዓ.ም በብሩንዲ(ምስራቅ አፍሪካ)ቢዝነስ እና ንግድን በአፍሪካ ውስጥ እንዲሁም በሌሎች አህጉራት በመረጃ ቴክኖሎጅ መተግበሪያዎች የማሳደግ ራዕይን ይዞ የተዋቀረ ሀላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት ነው፡፡

በጥቅምት 2000 ዓ.ም፤ አፍሪሬጂስተር ኤስ.ኤ ከ ICANN(በ ኢንተርኔት አስተዳደር ላይ ሀላፊነት ያለው አለማቀፍ ድረጅት) ጋር ስምምነት የፈጠረ ሲሆን ይህም የICANN እውቀና የተሰጠው ሬጂስትራር ሆኖ ለመንቀሳቀስ ነው፡፡

አፍሪሬጂስተር የ ICANN እውቅና የተሰጠው 3ኛው የአፍሪካ ሬጂስትራር ነው፡፡ የተለያዩ የዶሜይን ስሞች ምዝገባ አገልግሎትን የሚሰጥ ሲሆን ይህም እጅግ ተወዳዳሪ በሆነ መልኩ በአብዛኛዎቹ የኢንተርኔት ከፍተኛ ደረጃ ዶሜይን ተቀጽላዎች፡ አጠቃላይ TLDS (.com,.net,.org,.info,.biz,.tv ፣ወዘተ) እንዲሁም በ ccTLDS የተመሠረተ የሀገር ኮድ በተለይም የአፍሪካ ccTLDS (.bi, .ci, .co.ke, .ug, .co.za, .sd, .rw, .cd, .co.mz, .td, .bj, .mw, .sl, ወዘተ).


ራዕይ እና ተልእኮ

ራዕያችን “የተማረ፣ የበለጸገ እንዲሁም ጤናማ አፍሪካ በ2023 ዓ.ም አድማስ መመልከት ነው”

ዛሬ አፍሪካ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ የICT እንዲሁም ICTን መሠረት ያደረጉ ጥቅሞች እና አገልግሎቶች ተጠቃሚ ናት፡፡ ተልእኮአችን በአፍሪካ ለሚደረገው የICT መስፋፋት ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በአፍሪካ ውስጥ ማበርከት እንዲሁም አሁጉሯን የሳይበር ጥቅሞች እና አገልግሎቶች ጥሩ የምርት እና የኤክስፖርት አቋም ላይ ማኖር ሲሆን ይህም የአፍሪካ ሕዝብ እድገት እና ደህንነትን በማጐልበት ነው፡፡


እንቅስቃሴዎች እና አገልግሎቶች

የአፍሪሬጅስተር ዋናው የእንቅስቃሴ መስክ ኢ-ኮሜርስ ሲሆን ዋና መ/ቤቱ በቡጁምቡራ ፣ ቡሩንዲ ሲሆን የሥራ ሂደት ንዑስ ክፍሎች በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እንደ ሩዋንዳ ፣ ኬንያ ፣ ቻድ ፣ ሱዳን፣ የኮንጐ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ታንዛኒያ ፣ ቡርኪናፋሶ ፣ አይቬሪኮስት፣ ቤኒን እና ሴኔጋል አሉት፡፡